በመዲናዋ ከ33 ሺህ በላይ ነጋዴዎች በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርተው በመገኘታቸው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገለጸ

0
730

ዕረቡ ሚያዝያ 5 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ33 ሺህ በላይ ነጋዴዎች በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርተው በመገኘታቸው ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አደም ኑሪ እንደገለጹት፤ 17 ሺህ 424 ማስጠንቀቂያ፣ 14 ሺህ 285 የታሸጉ፣ 260 የተሰረዘ ንግድ ፈቃድ፣ 107 የታገደ ንግድ ፈቃድ፣ 120 ከትስስር የወጡ ንግድ ድርጀቶች 1 ሺህ 495 ከተፈቀደው የልኬት መጠን በታች በመለካት ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

በርካታ የንግድ ማህበረሰብ አካላት በቅንነት እያገለገሉ የህብረተሰቡን ችግር ለማቃለል መስራታቸውንና ከ12 ሺህ በላይ የንግድ ድርጅቶችም ሚዛኖቻቸውን ወደ ዲጅታል መቀየራቸውን ተናግረዋል።

ቢሮው በቀጣይም ከንግዱና ከሸማቹ ማህበረሰብ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት ግንዛቤ በመፍጠርና ሕገ ወጥነትን የመከላከል ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡

የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የተለያዩ ሕግ የማስከበር ሥራ እየተሰራ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here