በመጭዉ የፋሲካ በዓል የዘይት አቅርቦቱ በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን እየሰራ መሆኑ ተገለጸ

0
366

ሐሙስ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) መጪውን የፋሲካ በዓል የዘይት አቅርቦትና ሥርጭት የግብይት ሰንሰለቱን በጠበቀና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲሰራጭ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮዉ ኃላፊ አደም ኑሪ ከዘይት አቅራቢ ድርጅቶች እና ባለ ድርሻ አካላት ጋር ዉይይት በተደረገበት ወቅት፤ የዘይት አቅራቢዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸውና የዘይትን ምርት ሥርጭት ከወዲሁ በሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት በኩል በአፋጣኝ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የአቅርቦትና የሥርጭት ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ያሳሰቡት አደም፤ ሥርጭቱ በተገቢዉ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑንም አክለው አስረድተዋል፡፡

የዘይት አቅራቢዎችም በበኩላቸው፤ በቢሮው በተቀመጠላቸው አቅጣጫ ለመስራትና ከወዲሁ ከፋሲካ በዓል በፊት በሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት በኩል ምርቱን ለማሰራጨት የጋራ መግባባት በመፍጠር ውይይቱ መጠናቀቁ ተገልጿል።

ቢሮዉ እንደ ስኳር እና ዘይት ያሉ ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦችም ለፋሲካ በዓል በተገቢው መንገድ ለነዋሪዉ እንዲደርሱ እየሰራ መሆኑም ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
_____________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here