ብሄራዊ ባንክ የባንክ ደንበኞች መረጃቸውን ወቅታዊ እንዲያደርጉ የሰጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ከ1 ወር ያነሰ ጊዜ እንደቀረው አስታወቀ

0
382

ሐሙስ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የባንክ ደንበኞች መረጃቸውን ወቅታዊ እንዲያደርጉ የተራዘመው የኹለት ወር ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ከ1 ወር ያነሰ ጊዜ እንደቀረው አስታውቋል።

ብሄራዊ ባንክ እኤአ በ27/08/2021 በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ኹሉም ባንኮች የደንበኞችን መረጃ አጣርተው እንዲያደራጁ መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህም መመሪያ የብሄራዊ ባንክ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ለተጨማሪ 2 ወር መራዘሙ አይዘነጋም።

ይኸው የተራዘመ የ2 ወር ጊዜ ሊጠናቀቅ ከ1 ወር ያነሰ ጊዜ እንደቀረው ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።

መረጃቸውን ወቅታዊ ያላደረጉ የባንክ ደንበኞች አቅራቢያቸው ወዳለ የባንክ ቅርንጫፍ መታወቂያ ይዞ በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ እንዲያደርጉ እና በመጨረሻ ቀን ላይ የሚፈጠር መጉላላት እና መጨናነቅ እንዲያስቀሩም ተጠይቋል።
_____________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here