መነሻ ገጽዜናየእለት ዜና2 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር የሚያወጣ አደንዛዥ ዕፅ በሻይ ቅጠል ደብቆ ለማዘዋወር...

2 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር የሚያወጣ አደንዛዥ ዕፅ በሻይ ቅጠል ደብቆ ለማዘዋወር የሞከረው ግለስብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ዕረቡ ሚያዚያ 12 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ግለሰብ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት በቁጥር 107 ፍሬ የሚሆን አደንዛዥ ዕፅ በሻይ ቅጠል ውስጥ በመደበቅ ለማዘዋወር በዝግጅት ላይ እያለ በቁጥጥር ሥር መዋሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ግለሰቡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል ተደርሶበት በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉም ነው የተገለፀው፡፡

ግለሰቡ በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ላምበረት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ አልጋ ይዞ እያለ፤ ከእነ አደንዛዥ ዕፁ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፤ ወደ አማራ ክልል ጎንደር አካባቢ በህዝብ ትራንስፖርት ለመውሰድ እቅድ እንደነበረው ታውቋል ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች