በመዲናዋ በነገው ዕለት ከ194 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የማዕድ ማጋራት መርሀግብር እንደሚያከናወን ተገለፀ

0
419

ዕረቡ ሚያዚያ 12 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት በመላው አዲስ አበባ ለሚገኙ ከ194 ሺህ በላይ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚኖሩ ዜጎች የማዕድ ማጋራት መርሀግብር እንደሚያከናውን አስታወቀ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ እንዳስታወቀው የማእድ ማጋራቱ በከተማ ደረጃ፤ በ11 ክፍለ ከተሞች፣ በ120 ወረዳዎች እንዲሁም በ6 ሺህ 885 ብሎኮች በተመሳሳይ ሰዓት የሚካሄድ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ጫና እና በተደራራቢ በዓልን ምክንያት በማድረግ ገቢ ሌላቸውና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለማስታወስና ለመደገፍ መርሀግብሩን ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

የማእድ ማጋራቱ ባለፉት ኹለት አመታት በተከታታይ ሲካሄድ የቆየና እርስ በእርስ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ፈታኝ ወቅቶችን የማለፍ እና መልካም ኢትዮጵያዊ እሴታችንን ለማዳበር ትልቅ ሚና እንዳለው መገለፁን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here