“የሩሲያ ኤምባሲ “ኤምባሲው የውትድርና ምልመላ ቅጥር አውጥቷል” በሚል የወጣውን መሠረተ ቢስ መረጃ ውድቅ ማድረጉ የሚደነቅ ነው” የኢትዮጵያ መንግሥት

0
524

ዕረቡ ሚያዚያ 12 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ የሚገኘው በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ “ኤምባሲው የውትድርና ምልመላ ቅጥር አውጥቷል” በሚል የወጣውን መሠረተ ቢስ ዘገባ ውድቅ ማድረጉ የሚደነቅና በመልካም የሚታይ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

ኤምባሲው ምንም አይነት የቅጥር ማመልከቻ እንደማይቀበል እና እ.ኤ.አ. በ 1961 የቪየና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነትን እንደሚያከብር ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከኤምባሲው ጋር ተስማምቶ የተገኘ ማንኛውም ቅጥር የቪየና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነትን የሚጥስ ሲሆን፤ ይህም የዲፕሎማቲክ ሚሲዮንን ተግባር የሚጻረር እንደሚሆን ይታወቃል።

የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምልመላ የኢትዮጵያን ህግ ከመጣሱም ባሻገር፣ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች የአገሩን ህግና ደንብ ለማክበርም ተደርጎ እንደታይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለወሰደው ፈጣን እርምጃ ኤምባሲውን እንደሚያደንቅም መግለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here