መነሻ ገጽማረፊያ10ቱ10 በእንቁላል ምርት ቀዳሚ አገራት

10 በእንቁላል ምርት ቀዳሚ አገራት

ምንጭ፡- ስታቲስታ (2020)

በዓል ሲዳረስ ይልቁንም ጾም ወቅት አልፎ የፍስክ ሰሞን ሲገባ፣ ገበያው ላይ ተፈላጊ ከሚሆኑ ምርቶች መካከል እንቁላል አንዱ ነው።
በኢትዮጵያ ውስጥ የፈረንጅ እንዲሁም የአበሻ ተብሎ ኹለት የዶሮ እንቁላል ዓይነት ሲቀርብ፣ በአውሮፓ አገራት ከዚህም ባሻገር የዶሮ ብቻ ያልሆኑና የተለያየ ቀለም ያላቸው እንቁላሎች ይገኛሉ። በአብዛኛውም ውስጣቸው ባለው ጥራት እና በውጪአዊ መልካቸው መሠረት ደረጃ ወጥቶላቸው የሚቀርቡበት ሁኔታም አለ።
ለቁርስ የሚዘወተረውና በአገራችንም በበዓል ሰሞን ለዶሮ ወጥ አንድ ግብዓት የሚሆነውን እንቁላል በብዛት በማምረት ቻይና ቀዳሚ አገር እንደሆነች ስታቲስታ በ2022 ባወጣው የ2020 የእንቁላል አምራቾች ዝርዝር ይጠቅሳል። ሕንድ እና ኢንዶኔዥያ ደግሞ ይከተላሉ። ይሁን እንጂ የምርት ልዩነታቸውን ስንመለከት፣ የተቀሩት የዘጠኙ የ2020 የእንቁላል ምርት ተደምሮ እንኳ ቻይና በዛው ዓመት ያመረተችው የእንቁላል መጠን ላይ አልደረሱም። መልካም በዓል!


ቅጽ 4 ቁጥር 181 ሚያዝያ 15 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች