መነሻ ገጽዜናየእለት ዜና“በኢትዮጵያ የሚሆነዉ ኹሉ ሌሎች አፍሪካዉያንንም ይመለከተናል”:- በኩዌት የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን አምባሳደር ሙሀመድ...

“በኢትዮጵያ የሚሆነዉ ኹሉ ሌሎች አፍሪካዉያንንም ይመለከተናል”:- በኩዌት የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን አምባሳደር ሙሀመድ ሳድ ኦሮሳማ

ዕረቡ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ የአፍሪካዉያን ኹሉ ቤት እንደመሆኗ በእርሷ ዉስጥ የሚከሰት ማንኛዉም ነገር በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ሌሎች አፍሪካዉያንንም ይመለከታል ሲሉ በኩዌት የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን አምባሳደር ሙሀመድ ሳድ ኦሮሳማ ተናገሩ።

በኩዌት የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሀሰን ታጁ በኩዌት የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን ከሆኑት ከቶጎ አምባሳደር ሙሀመድ ሳድ ኦሮሳማ ጋር ተገናኝተዉ ተወያይተዋል።

በዉይይት ወቅት አገራዊዉ ለዉጥ፣ በሰሜኑን የአገራችን ክፍል ያለዉ ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች፣ በአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ፤ በአፍሪካ አጠቃላይ የኢትዮጵያ በጎ ሚና፣ እንደዚሁም በህዳሴዉ ግድብ ድርድር ዙሪያ የኢትዮጵያን ፍትሀዊ አቋም ግድቡ ለቀጠናዊ ትስስርና ለአፍሪካ የልማት ግብ ያለዉ አስተዋፅኦ በአምባሳደር ሀሰን ተብራርቷል።

አምባሳደር ሙሀመድ በበኩላቸዉ የኢትዮጵያ የለዉጥ እንቅስቃሴ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት አርዓያ እንደሚሆን የተናገሩ ሲሆን፤ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተከሰተዉን ኹኔታ እንደተከታተሉና የሁኔታዎች መሻሻል እንዳስደሰታቸዉ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

አምባሳደር ሙሀመድ አክለውም “ኢትዮጵያ የአፍሪካዉያን ኹሉ ቤት እንደመሆኗ በርሷ ዉስጥ የሚከሰት ማንኛዉም ነገር በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ሌሎች አፍሪካዉያንንም ይመለከታል።” በማለት ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ጉልህ ስፍራና ሚና እንዳላትም ተናግረዋል።

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች