ዕረቡ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ሸዋልን በሐረር ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 3 ቀን 2014 በሐረር ከተማ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪን ተከትሎ ከተዘጋጁ መርሃ ግብሮች መካከል “ሸዋልን በሐረር” እና በጅግጅጋ ከተማ የሚካሄደው ‘አገረ መንግስት ግንባታና የዳያስፖራው ሚና’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሲምፖዚየም ይገኙበታል።
በጅግጅጋ ከተማ የሚካሄደው ሲምፖዚየም በመጭው ቅዳሜ ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፣ ሸዋልን በሐረር ደግሞ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት ቀን 3 ድረስ በሐረር ከተማ ይካሄዳል።
በዚህም ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የመጡ በመድረኮቹ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ዳያስፖራዎች ቀጥሎ በቀረቡት አድራሻዎች መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።
በስልክ ቁጥሮች (+251 965 34 55 33 ፤ +251 911 91 21 81 ፤ +251 911 46 55 30 ፤ +251 11 558 7473 ፤ +251 11 558 8355 ወይም በነጻ መስመር 9434) መደወል እንደሚችሉም ተገልጿል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n




