‹ታፕታፕ› የተሰኘው ዲጂታል ሃዋላ ሰጪ አገልግሎቱን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት አቅዷል

0
627

መሠረቱን እንግሊዝ ያደረገው ድርጅቱ ይፋ ያደረገው መተግበሪያ ዜጎችን ከየትም አገር ገንዘብ መቀብል የሚያስችል ሲሆን፣ እስከ አሁን ከቴሌ ብር፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ከዳሽን ባንክ ጋር ትስስር ፈፅሞ በሥራ ላይ ነው።
የድርጅቱ ሥራ ኃላፊዎች በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን መተግበሪያውን ከሁሉም የፋይናንስ ሰጪዎች ጋር ለማገናኘት ከባንክ ሥራ ኃላፊዎች ጋር ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ሄለን አመልጋ እንደተናገሩት፣ ድርጅቱ ለሚሰጠው የሃዋላ አገልግሎት ክፍያ የማያስከፍል ሲሆን ይህንንም ያደረገው ደንበኞችንም ለማበረታት በማለም ነው።
ደንበኞችን ለመሳብ በማለም ድርጅቱ አንድ ዶላር በ54 ብር በመመንዘር ወደ ኢትዮጵያ የሚልክ ሲሆን ይህም በአሁኑ ሰዓት ባንኮች ከሚገዙበት ዋጋ በኹለት ብር ገደማ ከፍ ያለ ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 183 ሚያዝያ 29 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here