10ቱ በዓለማችን ለእምነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡ አገራት

0
682

ምንጭ፡-‘ፒው ሪሰርች’፤ 2018

ፒው በተባለ ተቋም ባለፈው ዓመት በተደረገ ጥናት መሰረት ኢትዮጵያውን በዓለም ላይ ካሉ ከ160 በላይ አገራት ለሃይማኖት ከፍተኛ ቦታ የሚሰጡ ሕዝቦች መሆናቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ ሕዝቡን ይወክላሉ ለተባሉ ሰዎች በቀረበ ጥያቄ፤ 98 በመቶ ኢትዮጵያውያን እምነት በሕይወታቸው ትልቅ ትርጉም ያለው ነገር ነው ብለዋል።

በርግጥ ከዚህ ቀደምም በማዕከላዊ ስታስቲክስ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው 100 ሚሊየን ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ ውስጥ እምነት የሌላቸው ሰዎች ከኹለት በመቶ አይበልጡም። የዛሬ 12 ዓመት በፊት በተደረገው ሕዝብ ቆጠራ መሰረት፦ በአገሪቷ ካሉ ሕዘቦች ውስጥ 43 ነnጥብ 5 በመቶ የሆኑት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሲሆኑ 33 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ሙስሊም ናቸው። ወደ 18 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው።

ቅጽ 1 ቁጥር 17 የካቲት 30 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here