የኦሮሚያው ሰልፍ

0
559

ሰሞኑን አነጋጋሪና አነታራኪ ሆነው ከሰነበቱት ጉዳዮች መካከል በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተካሔዱት ሰልፎች ይጠቀሳሉ። ሰልፉ በእርግጥ በማን ተጠራና ግልፅ አጀንዳውስ ምንድነው የሚለው ላይ በዝርዝር የተባለ ነገር ባይኖርም ከአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በስፋት ተንፀባርቀውበታል። ይኸውም አዲስ አበባ በ2005 ዳግም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፍላጎት መዝግባ ስታስቆጥባቸው ለኖረችው ነዋሪዎቿ በ12ኛው ዙር የኮንዶሚኒየም እጣ ማስተላለፍ መርሀ ግብር 51 ሺሕ ገደማ ቤቶችን ማስተላለፏ ነው። ኮንዶሚኒየሙን ለመገንባት ሲባል በእርሻ ሥራ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ያፈናቀለችው ከተማዋ ካሳ ብትሰጥም በተለያየ ምክንያት ተፈናቃዮቹና ቤተሰቦቻቸው ለከፋ የምጣኔ ሀብትና ማኅበራዊ ችግር ተጋልጠዋል በሚል ያለ እጣ የኮንዶሚኒየም ቤት እንዲሰጣቸውም ወስናለች።

ይሁንና ‹‹ኮንዶሚኒየሙ የተገነባው ኦሮሚያ ውስጥ ነው›› በሚልና ቤቱም ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በእጣ ሊተላለፍ አይገባውም በሚል ተቃውሞ በኦሮሚያ ክልል በርካታ ከተሞች ሰልፍ ሲደረግ ታይቷል። ይህም በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ዘንድ መከራከሪያ ሆኗል። ክርክሩም ለአርሶ አደሮቹ ቤት መሰጠቱ ተገቢ ቢሆንም ‹ሰልፉ ግን ተገቢ ነው! አይደለም! የሚል ነው።

በአንድ በኩል የአዲስ አበባ አስተዳደር ቤቶቹን የገነባው ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ገብቶ ስለሆነ ለአዲስ አበባ አይገባም ሲባል በሌላ በኩል ኮንዶሚኒየሙ የተገነባው አዲስ አበባ ውስጥ ነው ቤት እንዲደርሰው ሲቆጥብ የኖረውም የከተማዋ ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢ ነው በሚል ውዝግብ አስነስቷል። ይህም የይገባናል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ቤቱ የደረሳቸውን ኢትዮጵያዊያን ስጋት ውስጥ ከቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 17 የካቲት 30 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here