በመዲናዋ እየጨመረ በመጣው የግንባታ ላይ አደጋ ሰዎች እየሞቱ ነው

0
495

ባለፈው ማክሰኞ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላፍቶ ሞል አካባቢ በግንባታ ላይ በነበረ ህንፃ ውስጥ በደረሰ አደጋ ኹለት ሰዎች ሲሞቱ አራት ሰራተኞች ቆሰሉ።

ማክሰኞ ጠዋት የደረሰው አደጋ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለ ህንፃ አሳንሰር (ሊፍት) ሥራ ላይ በተሰማሩ ሰራተኞች ላይ የሕይወትና አካል ጉዳት አድርሷል።

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን እንዳሳወቀው በከተማዋ የህንፃ ግንባታ ላይ አደጋ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ የ17 ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል። በአዲስ አበባ እየደረሱ ካሉ አደጋዎች የሰው ሕይወትን በመንጠቅም ቀዳሚው የግንባታ ዘርፍ ላይ እያጋጠመ ያለው አደጋ መሆኑን አሳውቋል።

በማክሰኞው አደጋ 16 ወለል ላለው ህንፃ አሳንሰር ለመግጠም ሲሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ላይ ባጋጠመው የመወጣጫ መደርመስ አደጋ ሕይወታቸው ያለፉትን ግለሰቦች አስከሬን ለማግኘት እስከ ምሽት 4፡00 ፍለጋ መከናወኑን ባለሥልጣኑ ገልጿል። አደጋው በተከሰተበት ቦታ የነበሩ ሰራተኞች ምንም ዓይነት የግንባታ ላይ ደኅንነት መጠበቂያ የቅድመ ጥንቃቄ መሣሪዎችን እንዳላደረጉም የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 20 መጋቢት 14 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here