መንግሥት ይቅርታ ጠየቀ

0
520

ከመንግሥት ሲጠብቁ የነበሩትን ሙሉ በሙሉ ባለማግኘታቸው ቅር የተሰኙ ኢትዮጵያዊያንን መንግሥት ይቅርታ ጠየቀ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የበዓለ ሲመታቸውን አንደኛ ዓመት በሚሊኒየም አዳራሽ ባከበሩበት እለት ባደረጉት ንግግር ሲጠብቁ የነበረውን ባለማግኝት ቅር የተሰኙ ኢትዮጵያዊያንን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ይሁንና ቅሬታው የሚመጣው ብዙ ከመጠበቅና መሻት እንጂ እሳቸው ባለመሥራታቸው እንዳልሆነ የገለፁት ዐቢይ ዓመቱን ሙሉ ያለድካም ኢትዮጵያዊያንን ስለማገልገላቸውም እንዲታወቅላቸው ጠይቀዋል፡፡

በቀጣይም ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ለማሻገር ከሕዝቡ ጋር እንደሚተባበሩ ያነሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ የምትክ አልባዋን ኢትዮጵያ አንድነት አጠንክሮ የመሔዱ የቤት ሥራ ትኩረት እንዲያገኝም ሕዝቡን ጠይቀዋል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያን ከሚያፈርስ አካሔድ ተቆጥቦ ሁሉም ለአንድ አገሩ መፃዒ እድገትና አንድነት እንዲተባበርም መክረዋል፡፡

በሚሊኒየም አዳራሹ መርሀ ግብር ሰባት ሺሕ ታዳሚ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም የተገኘው ከግማሽ በታች በመሆኑ የተዘጋጁ ወንበሮች ሳይቀር ተመላሽ መሆናቸውን የአዲስ ማለዳ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 22 የመጋቢት 28 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here