ለሴት ተመራቂ ተማሪዎች አዲስ በአርያነት መምራት መርሃ ግብር ተጀመረ

0
846

መሪ የተሰኘ በዓይነቱ አዲስ የሆነ ለሴት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የአመራር እና የሜንቶርሺፕ (በአርዓያነት መምራት) መርሃ ግብር በሩያን ሶሉሽን እና ከደረጃ ትብብር ባለፈው ሳምንት ሚያዚያ 5 በአዲስ አበባ ተመርቆ ተከፈተ። የሩሲያን ሶሉሽን መሥራች እና የቀድሞ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቢልለኔ ስዩም እና የማኅበረሰብ ጤና ባለሙያ እና የሕግ ባለሞያዋ ሰናዪት ፍስሃ (ዶ/ር) በተገኙበት የተከፈተው ይህ ፕሮግራም ለወጣቶቹ ልምድ ካላቸው ሴቶች ተሞክሮ መቅሰሚያ እንዲሆን ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

መርሃ ግብሩ የተነደፈው ለሦስት ዓመት ሲሆን የመጀመሪያው ዙር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሥር ካሉ የተለያዩ ኮሌጆች የተመረቁ 30 ሴት ተማሪዎችን የሚያካትት እንደሆነ ታውቋል። ለሦስት ወር በሚቆየው የክህሎት እና የእውቀት ሥልጠናዎችን የሚያካትተው ሥልጠና ላይም የሚያስፈልገውን ወጪም እንደሚሸፍኑ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 24 ሚያዚያ 12 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here