10ቱ ዜጎቻቸው በድሃ መንደር የሚኖሩባቸው አገራት

0
559

ምንጭ፡-የዓለም ባንክ

በተባበሩት መንግሥታት የደሃ መንደር ማለት ግለሰቦች ወይም ቤተሰቦች በአንድ ጣራ ሥር የሚኖሩበት ሲሆን የተለያዩ የአየር ጸባዮችን የሚቋቋም ጠንካራ ቤት ውስጥ ያለመኖር አንዱ መስፈርት ነው።

በቂ የሆነ የመኖሪያ ቦታ ሌላኛው መስፈርት ሲሆን በአንድ ክፍል ውስጥ ከ3 በላይ ሰዎች የሚኖሩበት ከሆነ፣ በቂ እና በተመጣጣኝ ዋጋ የውሃ አቅርቦት እንዲሁም በቂ የሆነ የንፅሕና መሰረተ ልማት ካልተሟላ ዜጎች በእነዚህ መንደሮች ውስጥ እንደሚኖሩ ይታመናል።

ይህ የንፅሕና መስፈርት አንድም በግል መፀዳጃ ቤቶች አሊያም በሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች መሟላት እንደለበት የተባበሩት መንግሥታት ይደነግጋል። በተጨማሪም በጉልበት ከሚደረጉ ከመኖሪያ ቤቶች የማፈናቀል ድርጊቶች ነፃ በሆነ መልኩ ዜጎች ካልኖሩ በደሃ መንደር ለመኖር እንደ አንድ መሰፈርት ይጠቀሳል።

በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ከስምንት ሰዎች አንዱ በደሃ መንደር የሚኖር ሲሆን ይህም ከጠቅላላው የዓለም ሕዝብ አንድ ቢሊዮኑ ለመኖር በማይመቹ መንደሮች ውስጥ ይኖራል።

ቅጽ 1 ቁጥር 27 ግንቦት 3 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here