‘ብሩህ ተስፋ ለሚታየው ልባም’

0
747

ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች በተለይም በፌስቡክ በከፍተኛ ደረጃ መነጋገሪያ ከሆኑትና የብዙዎችን ቀልብ ከሳቡት መካከል የአንበሳ ቢራን ወደ ገበያ መግባት ተከትሎ የተለቀቀው ʻብሩህ ተስፋ ለሚታየው ልባምʼ የተባለው ማስታወቂ ነው። ብዙዎችን በኹለት ጎራ አሰልፎ አነታርኳልና የቃላት ጦርነት ውስጥም ከትቷል።

አንዳንዶች ማስታወቂያው በከፍተኛ ደረጃ የታሰበበት ከመሆኑም ባሻገር በቀላሉ ግቡን መትቷል በማለት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ሐሳባቸውን ለማስረዳት ማስረጃ ሲጠቅሱ ሰዎች ዓይናቸውን ቲቪ መስኮት ላይ እንዲጥሉ፣ እንዲጠይቁ ፣ ምንድን ነው ብለው እንዲወያዩ ማድረጉን እንደስኬት ቆጥረውታል። ፋብሪካ ከፍቶ መሥራትም ለአገር ዘርፈ ብዙ ጥቅም መኖሩን መዘንጋት የለበትም በማለት የማስታወቂያውን ተቺዎች ሐሳብ አጣጥለውታል።

በሌላ በኩል አንዳንዶች ደግሞ ማስታወቂያውን በከፍተኛ ደረጃ ኮንነውታል። እንደዚህ ዓይነት አማላይ ማስታወቂያ በተለይ ዕድሚያቸው መጠጥ ለመጠጣት ያልደረሱትን ታዳጊዎችንና ወጣቶችን ቀልብ በከፍተኛ ደረጃ በመሳብ በሥነ ልቦናቸውም ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ሲሉ ሥጋታቸውንም አስተጋብተዋል። በተጨማሪም ማስታወቂያው የኅብረተሰባችን የሞራል ደረጃ ምን ያክል እንደላሸቀ አንድ ማሳያ ነው ሲሉም ተከራክረዋል። በመጠጥ ተስፋ እንዴት ይገኛል ሲሉም ይጠይቃሉ። ረዘም ባለ ግጥምም ትችታቸውን የሰነዘሩ ይገኙበታል። የአንዱን የግጥም አንጓ እነሆ፡-
ተስፋ – የሚታየው ልባም
አገር እንጂ – በርሜል አይገነባም

ቅጽ 1 ቁጥር 27 ግንቦት 3 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here