ኤግዚብሽን ማዕከል ለመጀመርያ ጊዜ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ተከራየ

0
446
  • ክፍያው ተገቢ አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች ቀርበውበታል

ኢዮሀ አዲስ መዝናኛ የ2012 አዲስ ዓመት የበዓል ዐውደ ርዕይ ለማዘጋጀት በተከፈተው ጨረታ ካለፈው ዓመት የ10 ሚሊየን ብር ጭማሪ ከሌሎች ሦስት ተጫራቾች የተሻለውን ዋጋ በማቅረብ ማሸነፉ ታወቀ፡፡ ድርጅቱ 32 ሚሊየን ብር በማቅረብ፣ እንዲሁም ገንዘቡን ከዐውደ ርዕዩ በፊት በማስገባት ያሸነፈ ሲሆን፣ በኹለተኛ ደረጃ ከቀረበው 28 ሚሊዮን ብር በከፍተኛ ልዩነት ለማሸነፍ ችሏል፡፡

ሚያዝያ 9/2011 በተከፈተው ጨረታ አራት ድርጅቶች የተሳተፉበት ሲሆን፣ ኢዮሀ 32 ሚሊየን ብር በማቅረብ በከፍተኛ ዋጋ አሸናፊ ሆኗል፡፡ ኹለተኛውን ደረጃ የያዘው ሀበሻ ዊክሊ 28 ሚሊዮን ብር ሲያቀርብ፣ ሴንቸሪ ፕሮሞሽን 25 ሚሊዮን በማቅረብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ እንዲሁም ደመረ ሕብረት ሥራ 21 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በማቅረብ ዝቅተኛውን ደረጃ አስመዝግቧል፡፡

እንደዚህ ዓይነት ትርዒት የከተማውን እና የንግዱን እንቅስቃሴ በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡ ሆኖም ግን ከሌላው ጊዜ በተለየ የ10 ሚሊየን ብር ጭማሪ ለመቀበል ይከብዳል፡፡ ይሁንና ይህ ትርዒት በርካታ ኩባንያዎችና ነጋዴዎች እንዲሁም ደግሞ ገዢዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ተፅዕኖ የሚፈጥር በመሆኑ፣ የተከፈለው የመግብያ ፋይናንስ ተገቢ አይደለም በማለት የሀበሻ ዊክሊ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አዶኒክ ወርቁ ለአዲስ ማለዳ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል፡፡

በ2007 ሀበሻ ዊክሊ የአዲስ ዓመት ዓውደ ርዕይ በ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ያዘጋጀ ሲሆን፣ በ2008 ሴንቸሪ ፕሮሞሽን በ20 ሚሊዮን ብር በማቅረብ የአዲስ ዓመት ዐውደ ርዕይን ማቅረቡ ይታወሳል፡፡ እንዲሁም በ2011 ኢዮሃ በ29 ሚሊዮን ብር እና በ2010 20 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በማቅረብ ዓውደ ርዕዩን አዘጋጅቷል፡፡ በ2012 የአዲስ ዓመትን ዓውደ ርዕይ ግብይትን ለማሻሻል ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ጭማሪ በማድረግ ሊያቀርብ እንደሆነ ታወቋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here