ባለቤታቸውን በሞት ያጡት ፈረንሳያዊት ቦይንግን ከሰሱ

0
806

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ መጋቢት 1/2011 ባለቤታቸውን በሞት ያጡ አንዲት ፈረንሳዊት የአሜሪካውን ቦይንግ ኩባንያ መክሰሳቸውን አስታውቀዋል።

ፈረንሳዊቷ ናዴዥ ዱብዋ-ሲክስ ቦይንግ ላይ የሚከፍቱትን ክስ ፍትሕ እስኪያገኙ ድረስ እንደማያቋርጡ ረቡዕ፣ ግንቦት 14 ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል።

“በባለቤቴ ጆናታን፤ በሦስት ልጆቼ አባት ሥም ከዓለማችን እጅግ ኀያል እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አንዱ የኾነው ግዙፉ ቦይንግን እከሳለሁ። ይህ ከጎልያድ ጋር የጀመርኩት ትግል ፍትሕ እስክጎናጸፍ ድረስ አይቋረጥም” ብለዋል። በቺካጎ አንድ ኬኒያዊ ክስ መመስረቱም የሚታወስ ነው።

ናዴዥ ቦይንግ በባለቤታቸው ጆናታን ሲክስ ላይ ላደረሰው ጉዳት 276 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ የጠየቁ ሲሆን ቦይንግ ስለገጠመው መተግበሪያ ለአብራሪዎች አግባብነት ያለውን መረጃ ባለመስጠቱ ወንጅለውታል።

ቅጽ 1 ቁጥር 29 ግንቦት 17 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here