በ‘ሪፐብሊክ ጋርዱ’ አባል ሕልፈት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

0
665

ባለፈው ሳምንት በቢሾፍቱ ከተማ በምሽት ክበብ ውስጥ በተከሰተ አምባጓሮ ምክንያት በመንገድ ላይ ሕይወቱ ባለፈው የሪፐብሊክ ጋርድ አባል ምክንያት ሽጉጥ ተኩሶ ሕይወቱ እንዲያልፍ አድረጓል የተባለው የክለቡ ባለቤት፣ የቤተሰብ አባላቱ እንዲሁም ቁጥራቸው ከ10 የማያንሱ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

በመጠጥ ቤት ውስጥ የጀመረው ግጭት ወደ መንገድ ላይ በመውጣት ለየቀድሞው የኦሮሚያ ፖሊስ አባል እና ሕይወቱ እስካለፈ ድረስ የሪፐብሊክ ጋርድ አባል ነበረው ወጣት ሞት ምክንያት መሆኑን በቢሾፍቱ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ያሉ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ አረጋግጠዋል። የምርመራ ቡድን የተወቀረ ሲሆን ተጠርጣሪዎችን በከተማው ፍርድ ቤት ቀርበው ጊዜ ቀጥሮ ተጠይቆ ፍርድ ቤቱም በፈቀደው ቀን መሰረት ምርመራ በመደረግ ላይ መሆኑም ታውቋል።

በከተማዋም ባለፈው ሳምንት ውጥረት መኖሩን እና ፖሊስም ከተማውን ሲጠብቅ እንደሚያመሸ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here