ኢሚግሬሽን ሕገወጥ የፓስፖርት ተግባር ላይ የተገኙ ሠራተኞቹን ለሕግ አሳልፎ ሰጠ

0
773
  • ግማሽ ሚሊዮን ፓስፖርት ወደ አገር ውስጥ መግባት ጀምሯል

በቅርቡ እንደ አዲስ የተዋቀረው የኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኹነት ኤጀንሲ በመሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሕገወጥ በሆነ መልኩ የፓስፖርት እደላ ሥራ ላይ ተሳትፈዋል ብሎ የጠረጠራቸውን ሰዎች ለሕግ አሳልፎ መስጠቱ ታወቀ። ላለፉት 9 ወራት የተፈጠረውን የፓስፖርት እጥረት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ግለሰቦች ከኤጀንሲው ሠራተኞች ጋር በመመሳጠር ሕገወጥ ተግባራት በመንሰራፋታቸው ኤጀንሲው እርምጃ እንዲወስድ እንዳስገደደው ታውቋል።

የኤጀንሲው ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደሳለኝ ተሬሳ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት የተጠረጠሩት ግለሰቦች በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ሲሆን የተፈፀመው ወንጀል ዝርዝር እንዲሁም የሕግ ሒደቱ ሲደርስ ዝርዝር መረጃ የሰጡ ይሆናል።

በተጨማሪም የግማሽ ሚሊዮን የፓስፖርት ወረቀቶች ግዢ ተፈፅሞ በርከት ያለ ቁጥር ያለው ወረቀት በቦሌ አየር ማረፊያ መድረሱን የኤጀንሲው ሕዝብ ግኙኝነት ዳይሬክተሩ አስተውቋል። በቂ ቁጥር ያለው ፓስፖርት ወደ ሃገር ውስጥ ከገባ በኋላ አሁን ያለውን መመሪያ በማሻሻል ፓስፖርት ለመገኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች እንደሚነሱም አክለው ገልፀዋል።

“ግብዓቱን የሚያቀርብልን ድርጅት በፍጥነት ሙሉ ለሙሉ እንዳስገባልን እየጠበቅን ሲሆን አስተማማኝ ቁጥር ያለው ፓስፖርት መያዛችንን እርግጠኛ ስንሆን እንደቀድሞው የፓስፖርት አሰጣጡን በጥቂት ጊዜ ውስጥ እናሻሽላን” ሲሉም አክለዋል።

አዲስ ማለዳ በኤጀንሲው ተገኝታ ባደረገቸው ቅኝትም የመስተንግዶ ቅልጥፍና መሻሻል መኖሩን እና አስፈላጊ እና አሳመኝ ማስረጃ ይዘው ለሚመጡ ተስተናጋጆች በደቂቃዎች ውስጥ እየተስተናገዱ መሆኑንም ታዝባለች።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውሰጥ ከ300 ሺሕ በላይ ፓስፖርት እደላ ተደርጓል ሲሉ የኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ደሳለኝ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

አዲስ ማለዳ በዘገበቸው የምርመራ ሪፖርት በኤጀንሲው ውስጥ ባሉ ሰራተኞች እንዲሁም በኤጀንሲው ደጃፍ ተንሰራፍተው ባሉ ደላላች አማከንነት የተለያዩ ህገወጥ አካሄዶችን በመጠቀም የ ፓስፖርት ለመግነት እንደሚደረግ ታወቆ ነበር። የተሌ መንግስታዊ ድርጅቶች እንዲሁም ጉዞ ወኪሎች ፓስፖርት ለማገኘት የሚያስፈለጉ ሰነዶችን ጉቦ በመቀበል በማዘጋጀት እጥረቱን ለዘርፈ ብዙ ዘረፋዎች ማዋላቸውንም ታዝባ ነበር።

ኢትዮጲያ ባገጠማት የውጪ ምንዛሬ እጥረት ምክኒያት ለመጠባበቂ የተያዘው ፓስፖረት ወረቀት ተሟጦ ጥቅም ላይ መበዋሉ እና አዲስ ገዝቶ ለማስገባትም በተፈጠረው ክፍተት የመለበጃ ፕላስቲኩን እና ፓስፖረት ወረቀቱን ማስገባት ሳይቻል ቆይቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here