ብሔራዊ ባንክ የባንኮችን ማስታወቂያ መቆጣጠር ሊጀምር ነው

0
600

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮች በተለያዩ ዘዴዎች የሚያወጡትን ማስታወቂያዎች የብሔራዊ ባንክ የመቆጣጠር መብት የሚሰጥ ሕግ ሐሙስ፣ ሰኔ 6 ፀደቀ። ባንኮች ከእውነታ በራቀ፣ አሳሳች ወይም የሌላን ጥቅም የሚጎዳ ማስታወቂያ ሲያወጡ ብሔራዊ ባንክ ማስታወቂያው እንዲቋረጥ፣ እንዲሻሻል ወይም እንዲሰረዝ ለማድረግ የተሻሻለው የባንክ ሥራ አዋጅ ፍቃድ ሰጥቶታል።

ባንኮች በየዓመቱ ለማስታወቂያ ብቻ ከ20 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ወጪ የሚያወጡ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ቅጽ 1 ቁጥር 32 ሰኔ 8 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here