በስሜን ተራሮች የችግኝ ተከላ ሊጀመር ነው

0
514

በስሜን ጎንደር ዞን በስሜን ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ 52 ሔክታር መሬትን በዛፍ ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ሥራ ሊገባ እንደሆነ ታወቀ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠንሳሽነት የተጀመረውን አገራዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመመርኮዝ በፓርኩ በዛፍ ለመሸፈን በዝግጅት ላይ እንደሆነ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወርቁ ለምለሙ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ጨምረው እንደገለፁት ከወራት በፊት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ አጋጥሞት ከ1 ሺሕ ሔክታር በላይ የፓርኩ ክፍል ጉዳት እንደደረሰበት ጠቁመው የታሰበው የችግኝ ተከላ በትንሹም ቢሆን የደን ሽፋኑን እንደሚመልሰው አስረድተዋል። በፓርኩ ውስጥ የሚከናወነው የችግኝ ተከላ በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ እንደሚጀመር የአዲስ ማለዳ መረጃ ያመለክታል።

ስሜን ፓርክ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ብርቅዬ ዋሊያ መገኛ መሆኑ ይታወቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 33 ሰኔ 15 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here