ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ አራት ተከሳሾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዲጠሩ ትዕዛዝ ተሰጠ

0
742

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሥልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም በሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ብሎ ክስ ከመሰረተባቸው 26 የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኞች መካከል ያልተያዙትን ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ 4 ተከሳሾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥሪ እንዲቀርብላቸው እና ትዕዛዙም ለፕሬስ ድርጅት እንዲፃፍ ትዕዛዝ ሰጠ።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሐምሌ 18 ፣23፣ 24 ፣25 እና ለ30 ተለዋጭ ቀጠሮ የያዘ ሲሆን የጋዜጣውን ጥሪ ውጤት ለመስማት እና የተሻሻለ የምስክሮች አቤቱታን ለመስማት ለሐምሌ ዘጠኝ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 33 ሰኔ 15 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here