የወተት እጥረት በአዲስ አበባ አጋጠመ

0
594

ባሳለፍነው ቅዳሜ ሰኔ 15/2011 በአማራ ክልል በተፈፀመ የ“መፈንቅለ መንግሥት” ሙከራ እና በአዲስ አበባም በተመሳሳይ በከፍተኛ የጦር አዛዦች የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ አራቱም የአዲስ አበባ በሮች በመዘጋታቸው ወተት እና የተለያዩ የወተት ተዋፅዖ እጥረት አጋጥሞ ነበር ። ይህንም ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ካፊቴሪያዎች እና መሰል አገልግሎት ሰጪዎች ባጋጠመው የወተት እጥረት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁመው እንደነበር የታወቀ ሲሆን፤ የገበያ አዳራሾችም ወተት እጥረቱ በግልፅ ከታየባቸው ቦታዎች ዋነኞቹ እንደሆኑ የአዲስ ማለዳ ባደረገችው ቅኝት ተረድታለች።

ይሁንና በአሁኑ ወቅት ነገሮች ወደ ቀደመው መረጋጋታቸው እየተመለሱ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ አዲስ አበባ የሚያስገቡት በሮች በመከፈታቸው መደበኛው የንግድ እንቅስቃሴ መጀመሩንና አጋጥሞ የነበረውም እጥረት ሊቀረፍ እንደቻለ ለማወቅ ተችሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 34 ሰኔ 22 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here