ኢትዮጵያ በየዓመቱ 9 ቢሊዮን ብር ታጣለች ተባለ

0
594

በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሔደው ሕገወጥ የግብይት ስርዓት አገሪቱ በየዓመቱ እስከ 9 ቢሊዮን ብር የሚደርስ ገቢ እንደምታጣ አንድ ጥናት አመለከተ። በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በምጣኔ ኀብታዊ ዘገባው የሚታወቀው ‘ዘ ኢኮኖሚስት መፅሔት’ ጋር በመተባበር ሰኔ 18/2011 በተዘጋጀውና አሕጉራዊ የንግድ እንቅስቃሴ ችግሮች መንስኤዎቻቸውና መፍትሔዎቹ ዙሪያ የመከረ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሒዷል።

በዚሁ ወቅት ላለፉት አምስት ዓመታት ከፖሊሲ አውጪው አካላትና ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር የጉምሩክ ኮሚሽን ያካሔደው ጥናት ቀርቧል። በዚህም ጥናት ላይ እንደተጠቀሰው በኢትዮጵያ ከሚካሔደው አጠቃላይ የአገር ውስጥ ግብይት ስርዓት ውስጥ 40 በመቶ ያህሉ በሕገወጥ መንገድ በሚገቡ ምርቶች የተያዘ በመሆኑ አገሪቱ በሕገወጥ የግብይት ስርዓት ምክንያት የምታጣውን ከፍተኛ ገንዘብ መሆኑ በጉባኤው ላይ ተመላክቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 34 ሰኔ 22 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here