በቤተ እስራኤላዊያን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ቀጥሏል

0
422

አንድ የእስራኤል ፖሊስ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊውን ወጣት ሰለሞን ተካን ከገደለ በኋላ፣ እርምጃው ያስቆጣቸው ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊውያንና ደጋፊዎቻቸዉ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የአደባባይ ሰልፍና ውግዘት ማሰማታቸውን የተለያዩ ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል።

ሰልፈኞቹ የመኪና መንገዶችን በመዝጋት፣ ጎማና መኪኖችን በማቃጠል ግድያውን አውግዟል። በግጭቱ 111 ፖሊሶች ሲቆስሉ፣ 136 ሰልፈኞችም በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሰልፈኛው ሕግ እንዲያከብር ተማጽነዋል።

በሰሎሞን ሞት ማዘናቸውን የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን ተመኝተው፣ ሕግን መሰረት ባደረገ መልኩ ችግሮቹ እንዲፍቱ ጠይቀዋል።

የእስራኤል ፖሊሶች ኢትዮጵያውያን እስራኤላዉያን ወጣቶችን ሲደበድቡ ወይም ሲገድሉ ይህ የመጀመሪያዉ አይደለም። ባለፈዉ ጥርም አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት በፖሊስ ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል። ግድያና ድብደባዉ ከዘር ጥላቻ የመነጨ እንደሆነ ብዙዎቹ ያምናሉ።

ቅጽ 1 ቁጥር 35 ሰኔ 29 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here