በሶማሌ ክልል በችጉኒያ ወረርሽኝ 203 ሰዎች ተያዙ

0
768

በኢትዮጵያ ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ምክንያት የኀይል ማመንጫ ግድቦች የውሃ መጠናቸው በመቀነሱ ምክንያት ከግንቦት ወር 2011 የመጀመሪያ ሳምንታት እስከ ሰኔ 30/2011 ድረስ እንደሚቆይ ቀን የተቆረጠለት የመብራት ፈረቃ ከወር በላይ ሊራዘም እንደሚችል ታወቀ። በኢትዮጵያ የሚሰራጨውን የኤሌክትሪክ ኀይል ከ38 እስከ 40 በመቶ የሚሸፍነው የግልገል ጊቤ ሦስት የኀይል ማመንጫ ግድብ ውሃ መጠኑ ከሚጠበቀው በላይ መቀነሱ ለችግሩ ትልቁ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሶ አሁን ባለበት ሁኔታ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር 13 ሜትር እንደቀነሰ ታውቋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ዝናብ መዝነብ የጀመረ ቢሆንም ግድቡ በአማካይ 40 ሳንቲ ሜትር ብቻ ከፍ ማለት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አያይዘውም ከ2011 በጀት ዓመት መጀመሪያ ወር ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር በ16 ሜትር ቀንሶ የነበረ መሆኑን አውስተው የበልግ ዝናብ ያስተካክለዋል ተብሎ ተጠብቆ እንደነበርና ሳይሆን እንደቀረ አስታውቀዋል። አሁን ባለው ሁኔታ ግን በየዕለቱ የ40 ሳንቲ ሜትር ጭማሪ ታሳቢ በማድረግ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር እኩል ስለሚሆን ያለ ስጋት ኀይል ማመንጨት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ በሌላ በኩል ደግሞ በየዕለቱ የሚታየው የውሃ መጠን ጭማሪ 40 ሳንቲ ሜትር መሆኑ ወደ ሚፈለገው አምናው ተመሳሳይ መጠን ጋር ለመድረስ ከአምስት ሳምንት ወይም አንድ ወር ከአንድ ሳምንት ያላነሰ ጊዜ እንደሚጠበቅበት ለማወቅ ተችሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሰኔ 24/2011 ለሕዝብ እንደራሴዎች 2011 በጀት ዓመት መንግሥት የሥራ አፈጻጸም ባቀረቡበት ወቅት ከመብራት ፈረቃ ጋር በተያያዘ ከፀጉር አስተካካዮች እስከ ዳቦ ጋጋሪ ድርጅቶች ትልቅ ችግር ውስጥ እንደገቡ እና ምሬታቸውንም እየገለፁ በመሆናቸው መንግሥት ይህን ነገር በዘላቂነት ለመፍታት ምን እንደሚሠራም ከምክር ቤት አባሉ ታምሬ ዱትሶ ጥያቄ ቀርቦባቸዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ ሲሰጡም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት አማራጭ ኀይል ዘዴዎችን መጠቀም ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልፀው ለጊዜው ግን አገሪቱ በውሃ ላይ የተመረኮዘ የኀይል ማመንጫ ተጠቃሚ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ችግኝ በመትከል ዓመቱን ሙሉ ዝናብ ሳያቋርጥ እንዲዘንብ ማድረግ እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 35 ሰኔ 29 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here