ለውጪ ገበያ የሚቀርብ ከ58 ሺሕ ኪ.ግ በላይ ቡና ተዘረፈ

0
573

በያዝነው ዓመት ወደ ውጪ በመላክ ላይ የነበረ ከ58 ሺሕ ኪሎ ግራም በላይ ቡና በመንገድ ላይ መዘረፉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ አስታወቀ። እነዚህ ቡናዎች የተዘረፉት ከአምስት ድርጅቶች ብቻ መሆኑንም ገልጿል።

ባለቤትነቱ የአቦሀ ትሬዲንግ የሆነ 6 ሺሕ 360 ኪሎ ግራም ቡና ከጅቡቲ ወደ ጃፓን ሲላክ መዘረፉን ለአዲስ ማለዳ ያስታወቀው ቢሮው፤ ዱብዳ አግሮ ኢንዱስትሪ ከተባለ ቡና ላኪ ድርጅት 10 ሺሕ ኪሎ ግራም እና ቴሲቲ ትሬዲንግ 2 ሺሕ 500 ኪሎ ግራም ቡና መዘረፋቸውን አስታወቋል።

በተያያዘም ንብረትነቱ ኩሩ ኢትዮጵያ ኮፊ ዴቨሎፕመንት ሆነ ቡና ላኪ ድርጅት 39 ሺሕ 900 ኪሎ ግራም የታጠበ የሲዳማ ደረጃ ኹለት የሆነ ቡና ግንቦት 19/2011 በኹለት ኮንቴይነር ተጭኖ ወደ ጅቡቲ በመጓዝ ላይ እንዳለ በሞጆና አዳማ መካከል በሚገኝ ቦታ ላይ በዘራፊዎች ከነመኪናው መወሰዱንም ቢሮው አክሎ ገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 36 ሐምሌ 6 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here