“ካልቆሙ እርምጃ ውሰዱባቸው” እውነት ይሆን?

0
437

ከሳምንታት በፊት የአዲስ አበባ አስተዳደር እኔ ከሰጠሁት እውቅና ባለኹለት እግር ሞተር ተሽከርካሪዎች ከሰኔ 30/2011 ጀምሮ በአውራ ጎዳናዎቼም ሆነ በውስጥ ለውስጥ መንገዶቼ ላይ ውር ውር ማለት የተከለከለ ነው ሲል የእግድ ትዕዛዝን ማውጣቱን ተከትሎ የዛ ሰሞን መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል። ሞተረኞቹም “ግብታዊ” ያሉትን የአስተዳደሩን እርምጃ በመቃወም በዛው ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውም እንዲሁ።

የፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ለዓመታት አስጠንቸዋለሁ ያለውን ጥናት ዋቢ በማድረግ የከተማው አስተዳደር እርምጃ ለመውሰዱ እንደ አንድ ምክንያት ይጠቅሳል። ይኸውም በጣም ብዙዎቹ ባለኹለት እግር ተሸከርካሪ ሞተሮች በሕገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ናቸው፤ የሚመለከተው የመንግሥት አካልም አያውቃቸውም። በኹለተኛ ደረጃ ደግሞ ሞተሮች በንግድ ሥራ ላይ ለመሠማራት የሚፈቅድ የሕግ ማዕቀፍ የሌላቸው መሆኑም ተጠቃሽ እንደ ሰበብ አስቀምጧል።

በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማዋን ነዋሪዎች ሰላምና ደኅንነት ፈተና ላይ ከጣሉት ወንጀሎች መካከል በሞተር ሳይክል እገዛ የሚፈጸሙት ወንጀሎች በግንባር ቀደም ናቸው። ሰሞኑን ፈቃድ ከተሰጣቸው ውጪ የእነዚህን ባለኹለት እግር ሞተር ሳይክሎች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ማሽከርከር ክልከላን ተከትሎ ተሰጠ የተባለው ትዕዛዝ ነዋሪዎችን በሰፊው አነጋግሯል። በርግጥ ፈቃድ ሰጪ የተባለው አካል መንግሥት ወይም የከተማ አስተዳደሩ ከሚል ድፍን ያለ ምላሽ ውጪ በግልጽ የተጠቀሰ የመንግሥት አካል የለም።

ተሰጠ የተባለው ትዕዛዝ ፈቃድ ሳይኖራቸው የተገኙ የሞተር አሽከርካሪዎች በመጀመሪያ እንዲቆሙ፣ ትዕዛዙን ሳይቀበሉ ማሽከርከራቸውን የሚቀጥሉ ወይም ለማምለጥ የሚሞክሩ ከሆነ የኀይል እርምጃ እንዲወስዱ ለጸጥታ አካላት መመሪያ ወርዷል የሚለው ጉዳይ ነው።

አንዳንዶች መንግሥት “ካላበደ” በስተቀር እንደዚህ ዓይነት እርምጃዎች እንዲወሰድ አይፈቅድም በማለት ሙግት የገጠሙ ሲሆን ሌሎች በበኩላቸው መመሪያው ወርዷል ሲሉ ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ። እነዚህኞቹ ክርክራቸውን በማስረጃ ሲያስደግፉ ባለፈው ሳምንትና በዚህኛውም ሳምንት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሞተረኞችና ከሞተሮቹ ላይ የተፈናጠጡ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት መሞታቸውን ያነሳሉ።

ብዙዎች ግን ግራ በመጋባት ላይ ናቸው። እውነት ግን “ካልቆሙ እርምጃ ውሰዱባቸው” ተብሎ ይሆን እንዴ?

ቅጽ 1 ቁጥር 36 ሐምሌ 6 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here