ምፅዋን ከኢትዮጵያ የሚያገናኘው መንገድ በመጠናቀቅ ላይ ነው

0
665

ከኤርትራ ወደብ ከተማ ምፅዋ በመነሳት እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ድረስ የሚዘልቀው መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው። የመንገድ ግንባታው ከዚህ ቀደም የነበረውን የገጠር ጠጠር መንገድ የማሻሻል ሥራ ሲሆን በርካታ ኪሎ ሜትሮችንና ከተማዎችን እንደሚያቋርጥ ታውቋል። በኹለቱ አገራት የሚኖረውን የንግድ እና ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ወደ ተሻለ ደረጃ ያደርሳል ተብሎ የታቀደለት የመንገድ ግንባታው ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶችና መዳረሻዎች በተለየ ሁኔታ ጥገና እየተደረገላቸው እንደሆነም ኤርትራ ፕረስ አስነብቧል።

ከነፋሲት- ደቀ መሐሪ 40 ኪሎ ሜትር፣ ከቀደ መሐሪ – ተራ ዕምኒ 29 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከአዲቋላ – እንዳ ገርግስ 18 ኪሎ ሜትር መንገዶች በዋናነት እየተገነቡ እንደሆነ ታውቋል። የመንገድ ግንባታው በዋናነት በአውሮፓ ኅብረት ለአፍሪካ ከሚሰበስበው ‹ትረስት ፈንድ› እንደሆነ ተገልጿል። በኹለተኛው የግንባታው ምዕራፍ የአስፓልት ማልበስ ሥራ እንደሚሠራም ኤርትራ ፕረስ ጨምሮ ዘግቧል።

ቅጽ 1 ቁጥር 37 ሐምሌ 13 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here