በአሜሪካን የኢትዮጵያን መንግሥት የሚቃወሙና የሚደግፉ ሰልፎች ተካሔዱ

0
500

ሐሙስ፣ ሐምሌ 11 በዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ‹‹ኢንተርናሺናል ድራይቭ›› በተሰኘው ጎዳና ላይ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚያወግዙ እና የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሒደዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚመራውን መንግሥት የተቃወሙት ሰልፈኞቹ መንግሥት በአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አመራሮችና ደጋፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ተቃውመዋል። አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ቆይታው ፈጽሟቸዋል ያሏቸውን በደሎችም ሲያሰሙ ተስተውሏል።

በአንጻሩ በአገር ቤት ያለው አስተዳደር “ኢትዮጵያ ወደ ሰላም እና ዲሞክራሲ እንድትሻገር” እየተጋ ነው ያሉ ሰልፈኞች፣ ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡትን ወቅሰዋል።
ሰልፈኞቹ፣ የሕሊናና የፖለቲካ እስርኞች ይፈቱ፣ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ማስፈራሪያና እስርና በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ እየደረስ ያለው እስር፣ ወከባና ኢፍትሐዊ እርምጃ እየተበራከተ መሔድ የወደፊቱን ተስፋ የሚያጨልም ይሆናል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ስንቃወም የነበረው ስርዓት ዳግም እየተመለሰ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ከመሩት ሰዎች መካከል ኤርሚያስ ለገሰ ይገኙበታል።

ዐቢይ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በአሜሪካ ኢትዮጵያ ኤንባሲ የተቃውሞ ሰልፍ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 37 ሐምሌ 13 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here