በአገር ዐቀፍ ደረጃ ከሚተከለው ችግኝ ግማሹ በአማራ ክልል ውስጥ ይተከላል

0
680

በሐምሌ 22/2011 በአገር ዐቀፍ ደረጃ እንዲተከል ዕቅድ ከተያዘለት 2 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ውስጥ 100 ሚሊዮን የሚሆነው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ እንደሆነ ታወቀ። የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ጌታቸው እንግዳየሁ ከአማራ ብዙኀን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ በክልሉ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተው እየተተከሉ እንደሚገኙ እና በሐምሌ 22 በአንድ ቀን ዓለም ዐቀፍ ክብረ ወሰን ለመስበር በታቀደው መሰረት ለመተከል ከታሰበው 2 መቶ ሚሊዮን ችግኝ ግማሹ በክልሉ እንደሚተከል አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ በ2011 ክረምት ወራት 4 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ የተያዘ ሲሆን፤ ይህንንም ለማሳካት በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ ተከላው ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። በሐምሌ 22 የሚደረገው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም የዚሁ አካል ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 37 ሐምሌ 13 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here