ዘመቻ ሙሴ በፊልም ሊመጣ ነው

0
922

ኢትዮጵያ በእርስ በርስ ጦርነት በምትታመስበት ወቅት በርካታ ቤተ እስራኤላዊያንን ከሱዳን ወደ እስራኤል ለማሻገር የተደረገው ዘመቻ በአሜሪካው የመዝናኛው ኢንዱስትሪ ሥመ ጥሩ ኩባንያ ‹ኔት ፊሊክስ› ተሠርቶ መጠናቀቁ ከወደ አሜሪካ ተሰምቷል። ‹ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት› በሚል ርዕስ የተሠራው ፊልሙ፤ የጌዲዮን ራፍ ድርሰት ሲሆን በዚህ ሐምሌ 2011 መጨረሻ ላይ ለዕይታ እንደሚበቃም ፊልሙን የሠራው ኩባንያ ይፋ አድርጓል።

የእስራኤልን የስለላ ድርጅት ሞሳድን ጀብደኛ እንቅስቃሴዎችን በስፋት የሚዳስሰው ይህ ታሪካዊ ፊልም በጊዜው በዘመቻው ወቅት 200 ቤተ እስራኤላዊያን በአንድ ጊዜ በሰባት ሳምንታት ውስጥ 30 በረራዎችን በማድረግ ከሱዳን በጊዜው እስራኤል መናገሻ ወደ ነበረችው ቴል አቪቭ የተጓጓዙበት ነበር።

የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት በርካታ ቤተ እስራኤላዊያን ቀናትና ሳምንታትን በእግራቸው ተጉዘው ከኢትዮጵያ የወጡ ሲሆን በአስቸጋሪው እና ፈታኙ የእግር ጉዞ ላይ ከ4 ሽሕ በላይ ቤተ እስራኤላዊያን በመንገድ ላይ እስከ ወዲያኛው አሸልበዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 37 ሐምሌ 13 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here