የኢትዮጵያ አየር መንገድ በታሪክ ከፍተኛውን የመንገደኛ ቁጥር አስተናገደ

0
623

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሐምሌ 10/2011 በታሪኩ ከፍተኛ ያለውን የመንገደኞች ቁጥር ማስተናገዱን አስታወቀ። በዚሁ ቀን 310 በረራዎችን ከመላው ዓለም ወደ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ እና ከቦሌ አየር ማረፊያ ወደ ተለያዩ አየር መንገዱ መዳረሻዎች ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል።

ከተደረጉት 310 ዓለም ዐቀፍ በረራዎችም 29 ሺሕ አምስት መቶ ኻያ ስምንት ገቢና ወጪ መንገደኞች መስተናገዳቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል። ከእነዚህም ውስጥ 21 ሺሕ ኻያ ስምንት የሚሆኑት ከአገር የሚወጡ መንገደኞች ሲሆኑ፤ ቀሪ 8 ሺሕ 500 መንገደኞች ደግሞ ከተለያዩ ዓለም ዐቀፍ አገራት ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ነበሩ።

የቦሌ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ ዳይሬክተርና ተጠባባቂ ሥራ አስፈፃሚ ጌታነህ አደራ እንዳስታወቁት፤ በከፊል አገልግሎት መስጠት የጀመረውን አዲሱን የመንገደኞች ማስተናገጃ ተከትሎ የሚስተናገደውን የመንገደኛ ቁጥር እጥፍ በማድረግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን መንገደኛ በዚሁ የክረምት ወር ለማስተናገድ በመቻላቸው ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 37 ሐምሌ 13 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here