10ቱ ከሕዝብ ቁጥራቸው አንጻር ብዙ ሲጋራ አጫሾች ያለባቸው አገራት

0
625

ምንጭ: ስፔክታተር ኢንዴክስ 2019

የዓለም የጤና ድርጅት ከአራት ዓመታት በፊት ባደረገው ጥናት በዓለማችን አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን የሚሆነው የተለያዩ ዓይነት የትንባሆ ዓይነቶችን የሚያጨስ ሲሆን ከዚህ ውስጥም ሴቶች እጅግ ያነሰ የሚባል ድርሻ እንዳለቻው ይፋ አድርጎ ነበር። በዓለማችንም የአጫሾች ቁጥር መቀነስ እያሳየ ቢበጣም በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ እንዲሁም በተወሰኑ የእስያ አገራት ጭማሪ በማሳየት ላይ መሆኑንንም ሪፖርቱ ገልጿል።

ኢትዮጵያም ዝቅተኛ የሚባል የአጫሽ ቁትር ያላት አገር ሆና የተመዘገበች ሲሆን ከሕዝብ ብዛቷም ከ10 በመቶ በታቹ አጫሾች እንደሆነ የዓለቀማፉ የጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል። ሪፖርቱ አክሎም የሴት አጫሾች ቁጥር በኢትዮጵያ ከዜሮ በታች መሆኑን አስነብቧል።

የጤና ሚኒስቴርም በተለያዩ ወቅቶች የአጫሾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን በመጥቀስ ሕጎች እንዲጠብቁ እና የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ሕግ አውጪውን በመጎትጎት ላይ ይገኛል። የዚህ ውጤት የሆነውን ጥብ’ቅ የማጨሻ ቦታዎች ድንጋጌን ያዘው አዋጅ መጽደቅ ሲሆን በተጨማሪም የኤክሳይስ ታክስ ጭማሪ እስከ 70 በመቶ እንዲሆንም የጤና ሚኒስቴሩ የሕዝብ ተወካዮችን መጠየቃቸው ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 39 ሐምሌ 27 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here