ዐቃቤ ሕግ በቢኒያም ተወልደ ዋስትና ላይ ይግባኝ ለማለት 10 ቀን ተፈቀደለት

0
719
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ባልደረባ ለነበሩት ቢኒያም ተወልደ የዋስትና መብት መፍቀዱን ተከትሎ የዐቃቤ ሕግ የይግባኝ ሒደትን ለመጠባበቅ 10 ቀን ቀጠሮ ሰጠ።
ዛሬ፣ ሐምሌ 29/2011 ስምንት ሰዓት በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድ የበየነ ሲሆን ዐቃቤ ሕግም በፀረ ሙስና አዋጁ መሰረት ተከሳሽ የተከሰሱባቸው አራት ክሶች ሲደመሩ ከ10 ዓመት በላይ በመሆኑ የዋስትና መብት መፈቀዱ አግባብ አይደለም ሲል በጽሑፍ ተቃውሟል።
በሕጉ መሰረትም በውሳኔው ላይ ይግባኝ እላለሁ ያለው ዐቃቤ ሕግ ከፍርድ ቤቱ የውሳኔ ግልባጭ ለማውጣት እና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት 10 ቀን የተፈቀደለት ሲሆን ተከሳሽም እስከ ቀጠሮ ቀኑ ድረስ በማረፊያ የሚቆዩ ይሆናል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here