የሥራ ፈጠራን የሚያስተባብር ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋመ

0
247

ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒንስትሩ የሚመራ እና የሥራ ፈጠራን የሚያስተባብር ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቋመች። ብሔራዊ ኮሚቴው ዘላቂ የሥራ ዕድሎች የመፍጠር ጥረትን የማረጋገጥ ኀላፊነት እንደተጣለበት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የዘጠኙ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተሞች ከንቲቦች እንዲሁም ዐሥር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አባላት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት መረጃ እንደሚጠቁመው በየዓመቱ ከ2 እስከ 3 ሚሊዮን የሰው ኀይል ወደ የሥራ ፍለጋ ገበያውን ይቀላቀላል ተብሎ ይገመታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግማሽ ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት “ኤኮኖሚው እስካሁን በዓመት የሚፈጥረው የሥራ ዕድል ከአንድ ሚሊዮን እምብዛም አይዘልም” ሲሉ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ይሔንን ችግር ለመፍታት የሥራ ኮሚሽን ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ 2012 መጨረሻ ድረስ ለሦስት ሚሊዮን ዜጎች በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዷል። በዚህ ዓመት ግን የአገሪቱ ኤኮኖሚ የሥራ ዕድል የፈጠረው ለ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች ብቻ ነበር።

ቅጽ 1 ቁጥር 40 ነሐሴ 4 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here