የሂዩመን ራይትስ ዋች ዘገባ ባለስልጣናት በስደተኞች ላይ ስለሚፈጸመው በደል ግድ የላቸውም አለ

0
818

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ረቡዕ ነሐሴ 8/2011 ባወጣው መግለጫው፣ ቀይ ባህርን ወይም የኤደን ባህረ ሰላጤን በጀልባ አቋርጠው የመን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በሰው አሻጋሪ ደላሎች ለከፍተኛ ስቃይ እንደሚዳረጉ እና ባለስልጣናትም ስለሚፈፀመው በደል ግድየለሽ ናቸው ሲል አስታውቋል።

የተቋሙ መግለጫ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ ሰብዓዊ አያያዝ በጎደላቸው እስር ቤቶች እንደሚሰቃዩ አስታውቆ፣ የኢትዮጵያ የየመንም ሆነ የሳዑዲ አረብያ ባለሥልጣናት ስደተኞቹ የሚፈጸምባቸውን በደል ለማስቀረት እርምጃ ሲወስዱ አይታይም ብሏል።

ሥራ አጥነት እና ሌሎች ኤኮኖሚያዊ ችግሮች፣ ድርቅ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ባለፉት አሥርት ዓመታት ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን እና ሳዑዲ አረብያ ለመሰደዳቸው ምክንያት መሆናቸውንም አስታውቋል።

በዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት IOM ሪፖርት መሰረት፣ ሳዑዲ አረብያ ስደተኞችን የማባረር ዘመቻ በጀመረችበት እኤአ ህዳር 2017 ድረስ 500 ሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ አረብያ ነበሩ። ከግንቦት 2017 እስከ መጋቢት 2019 ባሉት ጊዜያትም ወደ 260 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ በግድ እንዲወጡ ተደርገዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here