የሶስተኛ ወገን መድኅን ዋስትና የምዝገባ ጊዜ ተራዘመ

0
600

በደቡብ ክልል ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ የተሸከርካሪዎች የሦስተኛ ወገን መድኅን ዋስትና ምዝገባ ለሦስተኛ ጊዜ ተራዘመ። የፌደራል መድኅን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በክልሉ የተከሰተው የፀጥታ ችግር የመድኅን ምዝገባውን እንዳስተጓጎለው አስረድቷል።

ኤጀንሲው ነሐሴ 9 እና 10/2011 በሀዋሳ ከተማ ከክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ጋር ባካሔደው ውይይት ምዝገባውን በሚመለከት በቴክኖሎጂ በኩል ቅድመ ዝግጅት ቢደረግም አሁንም አለመረጋጋቱ እልባት ስላላገኘ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል።

በውይይቱም እስከ ነሐሴ 30/2011 ድረስ መራዘሙ ተገለጸው ምዝገባው እስከ አሁን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ 168 ሽሕ ተሸከርካሪዎች ብቻ የሦስተኛ ወገን መድኅን በምዝገባ መፈፀማቸው ታውቋል። ይሁን እንጂ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ዘግይተው ለሚመጡ ተመዝጋቢዎች እንዲሁም የሦስተኛ ወገን ሳይዙ በሚያሽከረክሩ ግለሰቦች ላይ ቅጣት እንደሚጣል ውሳኔ ተላልፏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 41 ነሐሴ 11 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here