ከስፖርታዊ አደን 30 ሚሊየን ብር ተገኘ

0
608

ባሳለፍነው 2011 በጀት ዓመት በተደረገ የስፖርታዊ አደን 26 አዳኝ ቱሪስቶችን እና አብሮ ተገዦችን በማስተናገድ 1.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።

የውጭ ቱሪስቶች ለስፖርታዊ አደን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የማስተዋወቅ ስራዎች በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በሌሎች አሃጉሮች መከናወኑንም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ኝኙነት ባለሙያ ናቃቸው ብርሌው ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

አደኑ በሚካሄድባቸው ቀበሌዎች ለሚኖሩ አንድ ሺህ ሰዎች ከአደኑ በሚገኘው ገቢ በሚደረግ የገንዘብ ድጋፍ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ብርሌው ተናግረዋል።
ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማስፋትም በተያዘው የበጀት አመት መስሪያ ቤቱ እቅድ እንዳለው ተናግሯል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 42 ነሐሴ 18 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here