የሊድ-አሲድ ባትሪ አያያዝና ስርዓት ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ተገለጸ

0
980

በኢትዮጵያ ከአደገኛ ቆሻሻዎች መካከል የሚመደበው፣ በተሽከርካሪ ባትሪ ውስጥ የሚገኘውና ባለ-ሊድ አሲዳማ ባትሪ አወጋገድ ጥንቃቄ የተሞላበት ካልሆነ ከፍተኛ ችግር ያመጣል ሲል ያስጠነቀቀው የኢትዮጵያ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ነው።

በሁሉም ተሽከርካሪዎችና በፀሃይ ሃይል በሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ጥቅም ላይ የዋለውን የሊድ-አሲድ ባትሪ በማሰባሰብ እንደገና መጠቀም የሚቻልበትን መንገድ ለመዘየድ ወይም ለማስወገድ የሚደረገው እንቅስቃሴ፣ ደካማ መሆኑን ነው የኢትዮጵያ አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የገለፀው።

በኮሚሽኑ ፖሊሲ ህግና ደረጃዎች ጥናትና ዝግጅት ዳይሬክተር አየለ ኤገና ኮሚሽኑ ነሃሴ 15/2011 ከጀርመኑ የተራድኦ ድርጅት ጂአይዜድ (GIZ) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ውይይት ላይ እንደተናገሩት የሊድ አሲድ በአግባቡ ካልተያዘ ለሰው ጤና፣ ለአካባቢ ብክለት፣ ለብዝሃ ህይወት መዛባትና ለኢኮኖሚ ልማት እንቅፋት ይሆናል።

ቅጽ 1 ቁጥር 42 ነሐሴ 18 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here