ዓመታዊው የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በአዲስ አበባ ሊካሔድ ነው

0
760

በየዓመቱ የሚካሔደው እና ዘንድሮ ለስድስተኛ ጊዜ የሚደረገው ዓመታዊው  የኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ፎረም በኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ተባባሪ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሔዳል። ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፎረሙ በቀጣዩ ዓመት 2012 መስከረም ላይ እንደሚካሔድ የታወቀ ሲሆን በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል 3 መቶ ተሳታፊዎችን ከመላው አፍሪካ እንደሚያሳትፍም ይጠበቃል።

ከኢንተርኔት ነፃነት በአፍሪካ ጋር በተያያዘ  ከሚደረጉ ውስን መወያያ አጋጣሚዎች አንዱ የሆነውን ይህን ፎረም ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ በማዘጋጀቱ ትልቅ ኩራት እንደሚሰማው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ገልጿል። ፎረሙ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ምኅዳሩ ላይም ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here