ዳሰሳ ዘማለዳ ሰኞ ነሐሴ 27/2011

0
546

 

  • ኢትዮጵያ እና እስራኤል በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ኹለቱ ወገኖች በሳይበር ደኅንነት፣ በቴሌኮምኒኬሽ እና በጠፈር ሳይንስ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………..

  • የጀርመን ፓርላማ አባላት ከምክትል አፈ ጉባኤ ሽታየ ምናለ ጋር ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በማዘመን ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………

  • -በኢትዮጵያ በፍጆታ እቃዎች እና በአገልግሎቶች ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ግሽበትን ለመፍታት ከመንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ገልጿል። የዋጋ ግሽበቱ ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለውም ሲሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ዲኤታ እሸቴ አስፋው ገልፀዋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………

  • ዓመታዊው የአምባሳደሮችና ቆንስላ ኃላፊዎች ስብሰባ “ተቋማዊ ለውጥ ለላቀ ዲፕሎማሲ” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ነሐሴ 27/2011  በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሒልተን ሆቴል  እየተካሄደ ነው።ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ስድስት ቀናት ይቆያል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………..

  • -በመጪዉ አዲስ አመት ከመንግስት ዉጪ በህገ ወጥ መንገድ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ አካል እንዳይኖር አደርጋለሁ ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።(ቢቢሲ)

…………………………………………………….

  • የወላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ለጥያቂያችን ሕገ መንግስታዊ ምላሽ ይሰጠን ሲል አሳሰበ። ዛሬ ነሐሴ 27/2011 በሰጠው መግለጫም ወታደራዊ ዕዝ ጣቢያ ከወላይታ እና ከአካባቢዋ ይነሳ ሲልም ጠይቋል። (ዶቼ ቬለ)

……………………………………………………..

  • በእስራኤል አገር የሚገኘውን ኢትዮጵያ ገዳም ‹‹ዴር ሡልጣንን›› እናድን የሚል ጉባኤ በዋሽንግተን ተካሒዷል። (ቪኦኤ)

………………………………………………..

  • ኬንያ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ምንም አይነት ቋሚ የመንግሥት ሰራተኛ እንደማትቀጥርና ይህም የመንግሥትን ወጪ ለመቀነስ የታለመ እንደሆነ አስታውቃለች። (አብመድ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here