80 የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
981

የተለያዩ 17 የዓለም አገራት ዜግነት ያላቸው 80 የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በ2011 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ በቁጥጥር ሥር መያዛቸውን የፌደራል ፖሊስ የፀረ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ግብረ ኃይል አስታውቋል። ከግለሰቦች ጋር አብሮ የተያዘው የዕፅ መጠን 186 ኪሎ ግራም ኮኬይን፣ 9 ኪሎ ግራም ሔሮይን እንዲሁም 1ሽሕ አንድ መቶ አራት ኪሎ ግራም ካናቢስ መሆናቸውን ግብረ ኃይሉ ለኢዜአ ገልጿል።

የተያዙት አደንዛዥ ዕፆች በአብዛኛው በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ሦስተኛ አገራት ሊተላለፉ ሲሉ እንደሆነም ግብረ ኃይሉ አስታውቋል።በዕፅ ማዘዋወሩ ሒደትም በዋናነት የናይጀሪያ፣ ብራዚል፣ ቬንዙዌላ እና የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ቀዳሚ ተርታ ላይ ይገኛሉ። በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም 57 ዎንዶች ሲሆን 23 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here