የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ካልተሻሻለ በቀጠዩ ምርጫ እንደማይሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።

0
784

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በነሐሴ 18/2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ካልተሻሻለ በ2012 በሚካሔደው አገራዊ ምርጫ እንደማይሳተፉ ምክር ቤቱ አስታውቋል። 107 አባላት ያሉት የጋራ ምክር ቤቱ ውሳኔው 75 በመቶ የሚሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋም እንደሆነም ምክር ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

መንግሥት እንደገና መለስ ብሎ አዋጁን እንዲከልስ ያሳሰበው የጋራ ምክር ቤቱ ምንም ማስተካከያ ሳይደረግበት የቀጣዩን አገራዊ ምርጫ ማካሔድ ታአማኒነት እንደማይኖረው የጋር ምክር ቤቱ አሳስቧል። ጉዳዩን ለመመርመርም የጊዜ ችግር ካጋጠመ ምርጫ ጊዜው እንዲራዘም አማራጭ አቅርቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here