ዳሰሳ ዘማለዳ ማክሰኞ ነሐሴ 28/2011

0
603

1-በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ስር ለተሰማራዉ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል ላበረከተዉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አሚሶም ምስጋና አቅርቧል።ላለፉት አንድ ዓመት ኃላፊነቱን በሱማሊያ ሲወጣ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የሶማሊያ ሰላም እንዲሻሻል ከሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የሽብር ኃይሎችን ተጠራርገው እንዲወጡ  ከፍተኛ  ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።(ዋልታ)

…………………………………………

2-በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገሪቱ እየከፋ ከመጣው ዘረፋ እና ህገ ወጥነት ኢትዮጵያውያኑ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ። ኢምባሲው ኢትዮጵያዊያን በመደብራቸው ላይ የሚደረገውን ዝርፊያ ለመከላከል ለጥቂት ቀናት መዝጋት እንደሚኖርባቸው አሳስቧል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………

3- ኢትዮጵያ 14ኛውን የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ አሰፋፈር ጉባኤን ታስተናግዳለች። ጉባኤው ነገ ሐሙስ እና ዓርብ ነሐሴ 29 እና 30/2011 አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሔዳል። ጉባኤው በአፍሪካ ሲካሔድ ይሄ የመጀመሪያው ነው። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………

4- ኢትዮጵያ በ2011 በጀት ዓመት  ወደ ውጭ ሀገራት ከተላኩ የአበባ፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርት ከ9 ቢሊዮን 222 ሚሊዮን ብር  ማግኘቷን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡ከጠቅላላ ገቢው ውስጥ 7 ቢሊዮን 569 ሚሊዮን ብሩ ከአበባ፣ ቀሪው 1 ቢሊዮን 653 ሚሊዮን ብር ደግሞ ከአትክልት እና ከፍራፍሬ ምርት የተገኘ ነው፡፡የምርቶቹ  ዋነኛ መዳረሻዎችም ኔዘርላንድ፣ ሳዑዲ ዐረቢያ፣ እንግሊዝ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ኖርዌይ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች፣ ቤልጅዬም እና ጣሊያን እንደሆኑ ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

(አብመድ)

…………………………………………

5-የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ)፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን እና አባል አገራት በኢትዮጵያ ሳይንስና ሳይንሳዊ ባሕል ይጎለብት ዘንድ እገዛ እንዲያደርጉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጠየቀ፡፡ ጥያቄው የቀረበው ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል በተካሄደው የሳይንስና ዲፕሎማሲ የእራት ዝግጅት ላይ ነው፡፡ (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………

6- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት የሚገኘው ዓባይ ኅትመት እና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ በቀጣዩ ዓመት ምስጢራዊ ኅትመቶችን ሊጀመር እንደሆነ አስታወቀ። (አብመድ)

…………………………………………

7-1ኛው አገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ ዛሬ ነሐሴ 28/2011 በአዲስ አበባ   መካሄድ ጀመረ ።በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመካሄድ ላይ ባለው በዚህ ኮንፈረንስ በቱሪዝም ዘርፉ በሚስተዋሉ መልካም ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ያተኮረ ምክክር እየተካሄደ ይገኛል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………….

8- የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በደቡብ አፍሪካ የሚካሔደውን የዓለም የኢኮኒሚክ ፎረም ለመታደም ከሰዓታት በፊት ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ገብተዋል። (አብመድ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here