ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የጨርቃ ጨርቅ ማሽኖች አውደ ርዕይ ልታስተናግድ ነው

0
494

ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመት 2012 ከጥር 29 እስከ የካቲት 1/2012 የዓለም አቀፉን የጨርቃጨርቅ ማሽኖች አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች። የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤትና የዘርፍ ማኅበራት እንዳስታወቀው አውደ ርዕዩ በህንድ የጨርቃ ጨርቅ ማሽኖች አውደ ርዕይ ማኅበረሰብ የሚዘጋጅ ሲሆን ኢትዮጵያም አዘጋጅ አገር ሆና እንደትመረጥ ያስቻላት በዘርፉ እመርታ ካሳዩ አፍሪካ አገራት ቀዳሚ ሆና በመገኘቷ እንደሆነ ጠቁሟል።

በአውደ ርዕዩ ላይ ከ220 በላይ አለም አቀፍ ተሳታፊዎች እንደሚኖሩ የሚጠበቅ ሲሆን ከቻይና፣ ህንድ፣ ጣሊያን እና እንግሊዝ ከቀዳሚዎቹ ተሳታፊ አገራት ይጠቀሳሉ። አውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ መካሔዱ በአገሪቱ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here