ኢትዮጵያ በ2009 በጀት ዓመት 31 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር አጥታለች

0
878

በኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ተገቢውን ቁጥጥር እና ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት በ2009 በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 31 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር እንደ አገር እንደታጣ የጤና ሚንስትሩ ዶ/ር አሚር አማን አስታወቁ።

ከጠቅላላው አገር ውስጥ ምርት መጠን 1 ነጥብ 8 በመቶ ይሸፍናል የተባለው የኪሳራው መጠን የጤና ሚኒስቴር ከአለም የጤና ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ላይ የተሰራ የ15 ዓመት የኢንቨስትመንት ጥናታዊ ፅሁፍን በመመርኮዝ ያወጣው ሪፖርት ነው። በተለይም የልብና የደም ቧንቧ በሽታ፣ ካንሰር፣ የስኳር ህመም እና ሥር የሰደደ የመተንፈሻ አካላት በሽታ ያተኮረ የኢንቨስትመንት ኬዝ ሰነድ በዛሬ ነሐሴ 30/2011  ይፋ አድርጏል::

ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚተነብየው ተላላፊ ያልሆኑት በሽታዎች ላይ አሁንም ተገቢውን ቁጥጥር እና መከላከል ከተደረገ በቀጣይ 15 ዓመታት የ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎችን ህይወትና 64 ቢሊዮን ብር ማትረፍ እንደሚቻል አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here