ዳሰሳ ዘ ማለዳ አርብ ጳጉሜ 1/2011

0
1007

1-  መንግስት የተቋረጠውን ፈሳሽ የምግብ ዘይት ላይ የሚደረገውን ድጎማ በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀምር ተገለፀ። በተጨማሪ ለአዲስ ዓመት በዓል 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊትር ዘይት፣ 120 ሺህ ኩንታል ስኳር፣ 165 ሺህ ኩንታል ስንዴ፣ 100 ሺህ ኩንታል ጤፍ ለሸማቾች መዘጋጀቱን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ማህበርት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አሊ ተናግረዋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………..

2- የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ኸርማን ኮኸን ከዚህ ቀደም የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያን ተከትሎ ሰኔ 17/2011 የሰጡት አስተያየት ተገቢ ያልነበረ ነዉ በማለት ይቅርታ ጠየቁ። በወቅቱ “በአማራ ክልል የከሸፈዉ መፈንቅለ መንግስት የአማራን የበላይነት በኢትዮጵያ ለማምጣት የተደረገ ሙከራ ነዉ ”ብለዉ ነበር።(አዲስ ማለዳ)

…………………………………………..

3- አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም በቀጣይ 11 ወራት ሁለት ቢሊዮን ብር ለወጣት ስራ ፈጣሪዎች ለማበደር ማቀዱን አስታዉቋል። በተጨማሪም 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለተለያዩ ተበዳሪዎች ለመስጠት ያቀደ ሲሆን 15 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ማቀዱን ይፋ አድርጓል። (አዲስ ዘመን)

…………………………………………..

4- ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የህፃናት ማቆያ በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፓርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ስራ ጀምሯል። በቀጣይም መሰል የህፃናት ማቆያ ማዕከል በሌሎች ቅርንጫፎች እንደሚተገበርም ኮሚሽኑ አስታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………..……

5- የተለያዩ አሰቃቂ የምርመራ ድርጊቶች ሲፈጸምበት የነበረውን በተለምዶ ‹‹ማዕከላዊ›› ተብሎ የሚታወቀውን የወንጀል ምርመራ ጣቢያ ለጎብኝዎች ክፍት ሆነ።(ቪኦኤ)

…………………………………………..

6- “ጳጉሜን ወር ስለመንገድ ትራፊክ ደህንነት እንነጋገር” በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ ከጳጉሜ 1 እስከ ጳጉሜ 3 የሚቆይ የትራፊክ አውደ ርእይ ዛሬ  ተከፍቷል። በ2011 በሃገር አቀፍ ደረጃ 4 ሺህ 871 የትራፊክ አደጋ የደረሰ ሲሆን በዚህም አደጋ 4 ሺህ 597 የሞት፣ 7 ሺህ 407 ከባድ፣ 5 ሺህ 949 ቀላል አደጋ በአገሪቷ እንዳጋጠመ በመክፈቻ ስነ-ስርአቱ ተገልጿል።(ኤዜአ)

…………………………………………..

7- በባሕር ዳር ከተማ 19 ሽጉጥ እና  አንድ ክላሽንኮቭ ተያዘ። በህገ ወጥ መንገድ ተደብቀው ከተያዙት 19 ሽጉጥ እና አንድ ክላሽንኮቭ በተጨማሪ 3 ሺህ 427 መሰል ጥይቶችም ተይዘዋል። ህገ ወጥ የጦር መሳሪያው የተያዘው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሆኑም ነው የታወቀዉ።(አብመድ)

…………………………………………..

8- የቀድሞ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዚምባቡዌን ለ40 ዓመታት ከነፃነት ማግስት አንስቶ የመሩት ሙጋቤ ከየካቲት ወር ጀምሮ ሲንጋፖር በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው አረጋግጠዋል። (አዲስ ማለዳ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here